በኢትዮጵያ በምግብ ነክ ሸቀጦች ላይ 36.6 የዋጋ ግሽበት አጋጥሟል ተባለ፡፡

የብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ምክር ቤት የዘጠኝ ወራት የምጣኔ ሀብት አፈጻጸምን ገምግሞ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው፣ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ከፍተኛ ፈተና እየገጠመው ያለው ከዋጋ ግሽበት አንጻር መሆኑን ጠቁሟል።

በዚህም የዋጋ ግሽበቱ በዋናነት በምግብ ነክ ሸቀጦች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ መመዝገቡን ጠቅሶ፤ ይህም ካለፈው ዓመት የሚያዝያ ወር ጋር ሲነጻጸር የዋጋ ግሽበቱ 36.6 በመቶ መመዝገቡን አስፍሯል።

ምክር ቤቱ ጨምሮም ባለፉት ሦስት ዓመታት የዋጋ ግሽበትን ወደ ነጠላ አሐዝ ለማውረድ በርካታ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ጠቅሶ፣ ነገር ግን በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ሁኔታዎች ምክንያት የሚፈለገው ውጤት አልመጣም ብሏል።

ለዚህም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የጥሬ ዕቃዎች ዋጋ መናር፣ በአገር ውስጥ ያጋጠሙ ግጭቶች እና የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት የፈጠረው ዓለም አቀፍ የዋጋ ንረት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የዋጋ ግሽበት እንዲያሻቅብ ምክንያት መሆኑን አመልክቷል።

መንግሥት የዋጋ ግሽበቱን ለመቆጣጠር የተለያዩ እርምጃዎች እየወሰደ እንደሆነ የጠቀሰው መግለጫው፤ ከእነዚህም ውስጥ የመንግሥት ወጪን ከአገር ውስጥ ገቢ መሸፈን፣ የግብር ሥርዓቱን ማዘመን እና የተለያዩ ግብርን የተመለከቱ ማሻሻያዎች ማድረግ በቀጣይ ተግባራዊ ይሆናሉ ተብሏል።

ምንጭ፡- የብሔራዊ ማክሮ ኢኮኖሚ ምክር ቤት

ግንቦት 02 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *