የመንግስት መስሪያ ቤቶች በየአመቱ ለማስታወቂያ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ያደርጋሉ ተባለ፡፡

ሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤቶች መስሪያ ቤታቸውን እና ስራቸውን ለማስተዋወቅ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚያደርጉ ተነግሯል ፡፡

የመንግስት መስሪያ ቤት ሆነው ይህን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ ማውጣታቸውም ተገቢነት እንደሌለው ነው የኢትዮጵያ ሚዲያ ካውንስል የተናገረው፡፡

የካውንስሉ ምክትል ጸሀፊ አቶ አማረ አረጋዊ እንደተናገረው የመንግስት መስሪያ ቤቶች ይህንን ገንዘብ ማውጣታቸው ሳይሆን የሚያስገርመው ማስታወቂያቸውን የሚያስነግሩት በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ብቻ ነው ብለዋል፡፡

ይህ በመሆኑም የፍትሀዊነት ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ ገብቷል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የግል ወይም የንግድ መገናኛ ብዙሀን በፋይናንስ እጦት ከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸውም ነው የተጠቆመው፡፡

በመሆኑም የሚመለከተው የመንግስት አካል ማስታወቂያ የሚያስነግሩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ፍትሀዊ አሰራር መከተል አለባቸው ተብሏል፡፡

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከፍተኛ የገቢ ማሽቆልቆል ያጋጠማቸው የንግድ ወይም የግል ሚዲያ ተቋማትን ለመደገፍ መንግስት ውጤታማ አሰራር ሊከተል እንደሚገባም ተነግሯል ።

በሄኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 10 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *