የወባ ስርጭት ስጋት ባለባቸው የአማራ ክልል አምስት አካባቢዎች በሰዎቹ እጅ ላይ የሚገኘው የወባ መከላከያ አጎበር የአገልግሎትጊዜው ያለፈበት ነው ተባለ።

በአማራ ክልል አምስት አካባቢዎች የአጎበር መተኪያ ጊዜያቸው አልፎ ተቀያሪ ለማግኘት እየተጠባበቁ እንደሚገኙ የአማራ ክልል የወባ መካከል እና መቆጣጠር ፕሮግራም አሰተባባሪ አቶ ዳምጤ ላንክር ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በክልሉ አምስት አካባቢዎች ማለትም ሰሜን ሸዋ ላይ ( ሸዋሮ ቢት) ፣ እንሳሮ ፣ ደቡብ ወሎ ላይ ( ቃሎ) ፣ ማዕከላዊ ጎንደር እና ጎንደር ዙርያ መሆናቸውንም ለጣቢያችን አስታውቀዋል፡፡

አጎበር የሚተካላቸው እና የመተኪያ ጊዜው ያለፋቸው አካባቢዎች መኖራቸውን ለጤና ሚኒስቴር ማስታወቃቸውን እና መልስ እየጠበቁ መሆኑንም አቶ ዳምጤ ተናግረዋል።

ጤና ሚኒስቴርም ግዢወው ተፈፅሞ ቦርደር ላይ እንደሚገኝ በመግለፅ አስከ ግንቦት መጨረሻ እንደሚያገኙ እንደነገራቸውም ገልጸዋል ፡፡

በተያያዘም ማዕከላዊ ጎንደር እና ጎንደር ዙሪያ ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ደምቢያ ፣ ( ጣና ተፋሰስ አካባቢ) የወባ ስርጭት እየጨመረ መሆኑንም የክልሉ የወባ መካከል እና መቆጣጠር ፕሮግራም አሰተባባሪው አቶ ዳምጤ ላንክር አንስተዋል፡፡

አጎበር ለለማደል ፕሮግራም ከማመቻቸት ባሻገር ስርጭቱ ባየለባቸው አካባቢዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ እና መቆጣጠር በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ ለነዋሪዎች ስልጠና እየተሰጠ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል ፡፡

በረድኤት ገበየው

ግንቦት 11 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *