“ሊፍት ኢትዮጵያ” የትራንስፖርት ዘርፉን ተቀላቅያለሁ ብሏል፡፡

ሊፍት ኢትዮጵያ የታክሲ አገልግሎት በመዲናችን አዲስ አበባ አሁን ካለው የሜትር ታክሲ ክፍያ ከ25 እስከ 35 በመቶ ቅናሽ በማድረግ ለማህበረሰቡ አገልግሎት እንደሚሰጥ የሊፍት ኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ አቶ ሙኒብ አብዱልካፉር ተናግረዋል፡፡

አገልግሎቱ በመዲናዋ ያሉ አነስተኛ እና መካከልኛ ገቢ ያላቸውን የማህበረሰብ ክፍል የትራንስፖርት ፍላጎት ለሟሟላት መቋቋሙንም ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

አቶ ሙኒብ አገልግሎቱን የሚጠቀሙ ደንበኞች ክፍያውን የሚፈጽሙት በዲጂታል መሆኑ “ሊፍት ኢትዮጵያን” ለየት ያደርገዋል ብለዉናል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ አብረው መስራት የሚፈልጉ የተሸከርካሪ ባለንብረቶች፤ምንም ተቆራጭ( ኮሚሽን) የማይደረግባቸው ሲሆን፤
በወር የ449 ብር ጥቅል በመሙላት ብቻ ያለገደብ መስራት እንደሚችሉ ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡

አሁን ላይ 1 ሺ 800 መኪናዎች ከሊፍት ኢትዮጵያ ጋር አብረው እየሰሩ መሆናቸውን የነገሩን አቶ ሙኒብ፤በሚቀጥለው ወር 10 ሺ መኪናዎችን ወደ ስራ ለማስገባት ማቀዳቸውንም ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም “ሊፍት ተማሪ” የተባለ ለየት ያለ የተማሪዎች የወር ጥቅል የተዘጋጀም ሲሆን፤ተማሪዎች በጋራም ሆነ በግል በተመጣጣኝ ዋጋ የትራንስፖርት አገልግሎቱን እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡

አገልግሎት ፈላጎዎች “የሊፍት ኢትዮጵያን” መተግበሪያ ከጎግል በማውረድ አልያም በ9885 በነጻ የስልክ መስመር በመደወል መጠቀም ይችላሉ ተብሏል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን

ግንቦት 12 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *