በሳህል ቀጠና ከ18 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለከፋ ረሃብ ሊጋለጡ ይችላሉ ተባለ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው ሪፖርት እንዳመለከተዉ፣ በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ውስጥ በሳህል ቀጠና ከ18 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለከፋ ረሃብ ሊጋለጡ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል፡፡

መቋጫ የታጣለት የሩስያ እና የዩክሬን ጦርነት ደግሞ ይህ የከፋ ረሃብ እንዲከሰት ዋናዉ ምክንያት መሆኑን አስቀምጧል፡፡

በዚህም ለረሃብ የሚጋለጡ ሰዎች ቁጥራቸው እየጨመረ ከመጣ እና ሰዎች መጎዳታቸው ከቀጠለ ካሉበት እንዲሰደዱ ሊገፋፋ ይችላል ብሏል፡፡

እንደ መንግስታቱ ሪፖርት በፈረንጆቹ ከ 2014 ጀምሮ ቡርኪና ፋሶ ፣ ቻድ ፣ ማሊ እና ኒጀር ከ 1.7 ሚሊዮን በላይ የሚጠጉ ዜጎች የከፋ የረጋብ እና የምግብ እጥረት ችግር ውስጥ እንደሚገኙ የአልጀዚራ ዘገባ ያመላክታል፡፡

ከነዚህ አካባቢዎች የመጡ በርካታ ዜጎች ደህንነት እና የተረጋጋ ኢኮኖሚን እናገኛለን በማለት ወደ ሰሜኑ የአውሮፓ ክፍል ለመጓዝ ከሚፈልጉ ስደተኞች መካከል እንደሚገኙም ተገልጿል።

በረድኤት ገበየሁ

ግንቦት 13 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *