ኢትዮጵያ የቻን ውድድር ማጣርያ ተጋጣሚዋን አውቃለች::

የ2022 የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ [ቻን] ውድድር በአልጄርያ አስተናጋጅነት ሲከናወን የማጣርያ ድልድልም በዛሬው ዕለት ወጥቷል።

በክፍለ አህጉራት ተከፍሎ የሚከናወነው ይህ የማጣርያ ውድድር ላይ፣ የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ [ሴካፋ] ሦስት ሀገራትን ወደ ዋናው ውድድር የሚያሳትፍ ሲሆን በወጣው ድልድል መሰረት ኢትዮጵያ በመጀመርያ ዙር ከደቡብ ሱዳን የምትጫወት ይሆናል። ይህን የማጣርያ ዙር ከተሻገረች ደግሞ ሩዋንዳን በሁለተኛው ዙር ትገጥማለች።

የጨዋታ ቀናትም የመጀመርያው ዙር የመጀመርያ ጨዋታ ከሐምሌ 15-17 ፣ ሁለተኛው ጨዋታ ከሐምሌ 22-24 ባሉት ቀናት ሲካሄድ የሁለተኛ ዙር የመጀመርያ ጨዋታ ከነሐሴ 20-22 ፣ ሁለተኛ ጨዋታ ከነሐሴ 27 እስከ 29/2014 እንደሚደረጉ ካፍ አስታውቋል።

የሀገር ውስጥ ሊግ የሚጫወቱ ተጫዋቾችን ብቻ የሚያሳትፈው ይህ ውድድር በኢትዮጵያ አቆጣጠር ጥር 2015 ላይ በአልጄርያ አስተናጋጅነት የሚካሄድ ሲሆን ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ በ2014 እና 2016 ውድድሮች ላይ ተሳታፊ እንደነበረች አይዘነጋም ።
ምንጭ፡- የኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌደሬሽን

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *