በብራዚል ከባድ ዝናብ ባስከተለው አደጋ ሳቢያ በትንሹ 79 ሰዎች ህይወታቸው መጥፋቱ ተሰማ፡፡

በሰሜናዊ ብራዚል ፔርናምቡኮ ግዛት በተከታታይ ቀናት በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ የጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ አጋጥሟል፡፡
ይህንኑ ተከትሎ የሃገሪቱ ጦር ተጎጂዎችን ለመርዳት እና የተረፉትን ከናዳ ውስጥ ለማውጣት በአካባቢው ተሰማርቷል፡፡

በተጨማሪም በአላጎስ ግዛትም የአንድ ሰው ህይወት የጠፋ ሲሆን በርካታ ዜጎችም የት እንዳሉ ማወቅ አልተቻለም፡፡
እንደ ፍራንስ 24 ዘገባ ከሆነ፣ 79 ሰዎች በአደጋው ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፣ የግዛቲቱ ነዋሪዎች እና የሃገሪቱ ጦር በጋር በህይወት ያሉ ሰዎችን እና አስክሬኖችን የማፈላለግ ስራዎችን እየሰሩ ይገኛል ተብሏል፡፡

አደጋው በአየር ንብረት መለዋወጥ ምክንያት የተከሰተ እና በብራዚል ከደረሱ አደጋዎች መካከል ከአስከፊዎቹ መካከል የተመደበም ነው፡፡

ቁጥራቸውን ለመግለፅ የሚቸግሩ በርካታ ሰዎች የደረሱበትን አላውቅም ያለው የሃገሪቱ የአደጋ ጊዜ ማስተባበሪያ መስሪያ ቤት ከ4ሺህ ያላነሱ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ በጎርፉ መወሰዳቸውን አስታውቋል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር
ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *