በአዲስ አበባ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለዉ የህንጻዎች የውጭ ቀለም አጠቃቀም መመሪያ፣ ታሪካዊና በቅርስነት የተመዘገቡ ህንጻዎችን አይመለከትም ተባለ፡፡

በአዲስ አበባ የህንጻዎች የውጭ ቀለም አጠቃቀም መመርያ ተግባራዊ የማይሆንባቸው ህንጻዎች አሉ ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የማስታወቂያ ፍቃድ መጠቀሚያ ዳይሬክተር አቶ ሔኖክ ረጋሳ፣ የህንጻዎች የውጭ ቀለም አተገባበር ተግባራዊ የማይሆንባቸው የህንጻ ግንባታዎች እንዳሉ ነግረዉናል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክልል ውስጥ በሚገነቡ የህንጻ ግንባታዎች ላይ የቀለም አጠቃቀም መመሪያው ተግባራዊ ከማይሆንባቸው ህንጻዎች መካከል ታሪካዊ የሆኑ እና በቅርስነት የተመዘገቡ ህንጻዎች በዋነኝነት ይጠቀሳሉ ነዉ ያሉት፡፡

እንደዚሁም በእምነት ተቋማት ለማምለኪያ አገልግሎት ብቻ እንዲውሉ በሚገነቡ ግንባታዎች፤በተጨማሪም አለም አቀፍ የቀለም ስታንዳርድ ያላቸው ማዕከላት ግንባታዎች፤ ዋና ዋናዎቹ ናቸው ብለዋል፡፡

የህንጻዎች የውጭ ቀለም አተገባበር ተግባራዊ ለማድረግ የዳሰሳ ጥናት መደረጉን የተናገሩት አቶ ሔኖክ፣ በዳሰሳው መሰረት በፒያሳ፣ በአራት ኪሎ፣ በለገሀር እና በሜሲኮ አካባቢ የሙከራ ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡

መመሪያው አሁን ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ላይ ምክክር እየተደረገበት እንደሚገኝ ተገልጻል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ባዘጋጀው የህንጻ የውጭ ቀልም አተገባበር መመርያ ላይ የህንጻ ዲዛይን ባለሙያዎች እና አርኪቴክቶች ሀሳባቸውን የገለጹ ሲሆን፣ መመሪያው አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረው ባተጋባበሩ ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
ሪሌ እስቴቶች፡ ለአፓርትመንቶቻቸው ራሱን የቻለ አንድ ስታንዳርድ የህንጻ የውጭ ገጽታ ቀለም እንዲሁም በተናጠል ለተሰሩ ቤቶች አንድ ወጥ ስታንዳርድ የህንጻ ግንባታ ቀለም በማቅረብ ማፀደቅ ይኖርባቸዋል ተብሏል፡፡

የፀደቀው ስታንዳርድ ቀለምም በሁሉም የሪል እስቴቱ ሳይቶች ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *