በአዲስ አበባ የሚገኘው የዩክሬን ኤምባሲ 98ኛ ቀኑን በያዘዉ የሩስያ ወረራ ከ689 በላይ ህጻናት ተጎድተዋል አለ፡፡

ኢምባሲው የሃገሪቱን ፕሬዝደንት ቮሎድሚዪር ዘለንስኪን ጠቅሶ እንዳስታወቀዉ የሩሲያ ወረራ ብሎ በገለጸዉ የሁለቱ ሃገራት ጦርነት ምክንያት ከ446 በላይ ህፃናት ጉዳትን ማስተናገዳቸውን እና 243 ህጻናት መገደላቸውን አስታውቋል፡፡

እንደ ኤምባሲው ገለጻ 139 ህፃናት የገቡበት አይታወቅም ያለ ሲሆን ይህም “ሩስያ የያዘቻቸውን አካባቢዎች አሃዝ እንደማያጠቃልል አስታውቋል፡፡

ሩስያ ዩክሬንን በልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ወረራ ከፈፀመችባት 98 ቀናት የተቆጠሩ ሲሆን በእነዚሁ ጊዜያት ዩክሬን በርካታ የሲቪሎች ጉዳትን አስተናግዳለች ብለዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡
በተጨማሪም ዩክሬን ከፍተኛ የመሰረተ-ልማት ውድመቶች መፈጸማቸዉንም በተለያየ ጊዜያት በተንቀሳቃሽ ምስል ለአለም አጋርታለች፡፡

በአብዱሰላም አንሳር

ግንቦት 25 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *