“በጤናዉ ዘርፍ ታማሚ ብቻ ሳይሆን የጤና ስርዓቱም መታከም ይገባዋል”—የጤና ሚንስትር ዴኤታ ዶር አየለ ተሾመ፡፡

የጤና አልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ለማሳደግ የሚቆጣጠር ስርአት እንደሚያስፈልግ ተነግሯል፡፡

ሚንስትር ዴኤታዉ ዶ/ር አየለ ተሾመ እናዳሉት ውጤታማ የሆነ የጤና ዘርፍ ለመገንባት በመጀመሪያ ለዘርፉ የሚመጥን አሰራር መዘርጋት አለበት፤ይህ ካልሆነ የጤና ባለሙያዎችን ቁጥር በማሳደግ ብቻ ሃገሪቷ በዘርፉ የምትጠብቀዉን ለዉጥ ማምጣት አስቸጋሪ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በጤና ተቋማት የሚያጋጥሙ የመድሃኒት አቅርቦት ችግር፣የመሰረተ ልማት ፍትሃዊ ተደራሽነት፣የአገልግሎት አሰጣጥ ጉድለት፣በዘርፉ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና ተያያዥ ችግሮች ተቆጣጣሪና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን አሰራር በመዘርጋት መቀነስ የሚቻል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

እነዚህ ላይ በትኩረት ካልተሰራ የጤና ባለሙያውም ሆነ የጤና ተቋማት ቁጥርን ብቻ በማሳደግ የአገልግሎት ጥራት ለመምጣቱ ዋስትና እንደማይሆን በንግግራቸዉ አንስተዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር የጤና አገልግሎት ጥራትን በአገር አቀፍ ደረጃ ለማስጠበቅ በርካታ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ የተናገሩት ሚንስትር ዴኤታዉ፣በቅድሚያ በስርዓት ግንባታ ላይ የማሻሻያ ፕሮጀክት ትግበራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በረድኤት ገበየሁ

ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *