በደቡብ ክልል ቡርጂ ልዩ ወረዳ በገበያ ስፍራ በተነሳ ግጭት አስር ሰዎች ተገደሉ፡፡

ግድያው ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ የተፈጸመው በልዩ ወረዳው ሶያማ ከተማ በሚገኝ የገበያ ሥፍራ ላይ ነው፡፡
ኤትዮ ኤፍ ኤም ከአከባቢ እማኞች እንዳረጋገጠው ከሟቾቹ በተጨማሪ 21 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

በሥፍራው ነበርን ያሉ የአይን እማኞች ለጣቢችን ባልደረባ መሳይ ገ/መድህን እንዳሉት፣ ግድያው በሰዎቹ ላይ የተፈጸመው ራቅ ባለ የገጠር ቀበሌ አንድ ሰው መገደሉን የሚገልጽ ወሬ በገበያው ውስጥ ከተሠራጨ በኋላ ነው፡፡

በደቡብ ክልል የቡርጂ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማሬ አለማየሁ፣ በልዩ ወረዳው ጥቃት መፈጸሙን ለጣቢያችን ገልጸው፣ አሁን በአካባቢው ያለውን ችግር ለመቆጣጠር የፌደራል እና የክልል ልዩ ሀይል መሰማራቱን ነግረውናል፡፡

የደቡብ ክልል የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አለማየሁ ማሞ ለጣቢችን እንዳሉት፣ በአከባቢው ከፍተኛ የሆነ የስራ አጥነት ችግር በተደጋጋሚ ግጭቶች እንዲነሱ እና እንዲባባሱ ምክንያት ሆኗል፡፡
የክልሉም ሆነ የፌደራሉ መንግስት ለዚህ ትኩረት እንዲሰጥም ጠይቀዋል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን
ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *