የሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ያሰጋቸው ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ አድርገዋል፡፡

ከሰሞኑ የኒውክሊየር መሳሪያ ጭምር ሙከራ እያከናወነች የምትገኘው የሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ሰላም የነሳቸው ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ ወታደራዊ ልምምድ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡

እንደ ነጩ ቤተመንግስት ከሆነ የሰሜን ኮሪያን ጠባጫሪ ድርጊት በቅርብ እየተከታተልን ነው ያለ ሲሆን፣ ከደቡብ ኮሪያ ጋር እየተደረገ ባለው ወታደራዊ ስልጠናም ስምንት የሚሆኑ ሚሳኤሎች መወንጨፋቸውንም አስታውቋል፡፡

በባህር ላይ እያካሄዱት ካለው ወታደራዊ ልምምድ ላይ የተወነጨፉት የባሊስቲክ ሚሳኤል ሙከራዎች ሃገራቱ ያላቸውን የመከላከል አቅም ለመመዘን የተካሄደ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

በ10 ደቂቃ ውስጥ ከ4 ቦታዎች ተተኩሰዋል የተባሉት ሚሳኤሎቹ ወደ ደቡብ ኮሪያ ምስራቃዊ አቅጣጫ የተምዘገዘጉ ሲሆን፣ ለቅዳሜው የሰሜን ኮሪያ የሚሳኤል ሙከራ አፀፋ መሆኑንም ኢንዲፔንደንት አስነብቧል፡፡

አሜሪካ የሰሜን ኮሪያን ወታደራዊ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተከታተለች እንደምትገኝ ያስታወቀች ሲሆን፣ በቀጠናው ካሉ አጋሮቿ ( ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን) ጋር በቅርበት እየሰራች እንደምትገኝም የነጩ ቤተመንግስት የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጄክ ሱሊቫን አስታውቀዋል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር

ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *