ኢራን፣ ግብፅና ሳዑዲ አረቢያ በእስረኞች ላይ ከፍተኛ የሞት ፍርድ ያሳለፉ ሀገራት መሆናቸውን አምነስቲ አሳውቋል፡፡

በፈረንጆቹ 2021 መጨረሻ ላይ በአለም ዙሪያ በትንሹ 28 ሺህ 670 ሰዎች የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው መሆናቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ትናንት ባወጣው ዘገባ ገልጿል፡፡
በዚህ ውስጥ ታዲያ ኢራን፣ ግብፅ እና ሳዑዲ አረቢያ ቀዳሚ ሆነዋል።

“በ2021 በ18 ሀገራት በአጠቃላይ 579 የሞት ቅጣት ተፈፅሟል፡፡
ድርጅቱ ይህንን ” ቢያንስ ከ2010 ወዲህ ሁለተኛው ዝቅተኛው የሞት ቅጣት” ነው ሲል ገልጾታል፡፡

የመብት ተሟጋች ድርጅቱ “በኢራን እና ሳውዲ አረቢያ ከ2020 ጋር ሲነጻጸር 20 በመቶ የሞት ቅጣት ጨምሯል፣ 483 ሰዎች ውሳኔው ተፈጽሞባቸዋል” ማለቱን ሚዲል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል።

እንደ አምነስቲ መረጃ “ግብፅ የሞት ፍርድን በመተግበር የመጀመሪያዋ የአረብ ሀገር ሆናለች”፤ ሳዑዲ አረቢያ ሁለተኛ ስትሆን በ2021 በድምሩ 65 የሞት ቅጣት ፈፅማለች።

የመብት ተሟጋቹ ሲያክል ሶሪያ ባለፈው አመት 24 የሞት ቅጣት በመፈጸም ሶስተኛ ደረጃ ስትይዝ ፤ በሶማሊያ ከ21 በላይ የሞት ፍርድ ተፈፅሟል፣ ኢራቅ ከ17 በላይ ፣ የመን ከ14 በላይ እና ኦማን ቢያንስ አንድ ሰው ላይ ይህ የሞት ቅጣት ተፈፅሟል።”

የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ባለፈው አመት አንድ እስረኛ በሞት መቀጣቷን አምነስቲ ገልጿል። “በርካታ ሀገራት ባለፈው አመት የሞት ቅጣትን በጥቂቶች እና በተቃዋሚዎች ላይ በመተግበር ዝም ለማስባል ይጠቀሙበት ነበር” ሲል ዘገባው አክሎ ገልጿል።

በያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 01 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *