ህብረት ባንክ እድለኛ የሆኑ ደንበኞችን ተሸላሚ ያደረገ የእጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት በዛሬዉ እለት አከናውኗል።

ህብረት ባንክ በዛሬው እለት የሁለተኛው ዙር የይቆጥቡ፤ይቀበሉ ፤ ይመንዝሩ እና ይሸለሙ የእጣ አወጣጥ መርሃግብር በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ አከናውኗል።
በዚህ መርሃግብር ላይ በባንኩ ደንበኛ ለሆኑ እድለኛ ግለሰቦች ወደ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት ሽልማት በእጣ ወጥቷል።

15 የባንኩን ደንበኞች ተሸላሚ ያደረገው የሁለተኛው ዙር የይቆጥቡ፤ይቀበሉ፤ይመንዝሩና ይሸለሙ መርሃግብር ግብር ፤የቤት መኪና፤ባጃጆችን እና የተለያዩ ሽልማቶችን ያካተተ ነዉ፡፡

የባንኩ ስትራቴጂ እና ቴክኖሎጂ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አንዷለም ሃይል ባንኩ ከደንበኞቹ ጋር ያለዉን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ደንበኞች በመቆጠባቸው ተሻላሚ እያደረገ መሆኑንና ይህንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
የመጀመሪያዉ መኪና ተሸላሚ ቁጥርም 1343254 ሆኖ ወጥቷል፡፡

ከተመሠረተ ሁለት አስርት አመታትን ያስቆጠረዉ ህብረት ባንክ 7 ሽህ የሚሆኑ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን አጠቃላይ ካፒታሉም 54.1 ቢሊየን ብር ደርሷል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን

ሰኔ 02 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *