ኢትዮ ቴሌኮም የፓስፖርት አገልግሎት ክፍያዎችን በቴሌ ብር መፈፀም እንደሚቻል ይፋ አደረገ፡፡

ከበርካታ የመንግስት እና የግል ተቋማት ጋር ስምምነት እየፈፀመ የሚገኘው ኢትዮ ቴሌኮም አሁንም ከኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ጋር ስምምነቱን ፈፅሟል።

ስምምነቱም አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት፣ እድሳት ለመፈፀም እና ሲጠፋ ሌላ ለማውጣት አገልግሎት ሲፈልጉ በቴሌ ብር ክፍያ መፈፀም እንደሚችሉ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህወት ታምሩ አስታውቀዋል።

ወደ ተግባር ከገባ አንድ አመት ያስቆጠረው ቴሌ ብር 20 ሚሊዮን ደምበኞች እየተገለገሉበት መሆኑንም ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ጠቁመዋል።
20 ቢሊዮን ብር የገንዘብ ዝውውርም ተደርጎበታል ነው ያሉት።

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሙሉጌታ በበኩላቸው አገልግሎቱ በቀን ከ1500 እስከ 2000 የሚጠጉ ደምበኞች የሚስተናገዱበት መሆኑን ጠቅሰዉ አገልግሎቱን ለማግኘት የሚፈጠረውን መጨናነቅ ይቀንሰዋል የሚል እምነት እንዳላቸዉ ተናግረዋል፡፡

በረድኤት ገበየሁ

ሰኔ 02 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *