‹‹በአዲስ አበባ 80 የሚደርሱ የእሁድ ገበያዎች ተፈጥረዋል ›› ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ

‹‹በአዲስ አበባ 80 የሚደርሱ የእሁድ ገበያዎች ተፈጥረዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናግረዋል፡፡
በእነዚህ እሁድ ገበያዎች ደግሞ ከ 31 ዙር በላይ ሽያጭ ተከናውኗልም ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት በተደረገው እርምጃ የዳቦ አቅርቦት ላይ የተሰሩ ስራዎችን አንስተዋል፡፡
ቀደም ሲል ከነበሩት ዳቦ ፋብሪካዎች ተጨማሪ 10 ዳቦ ፋብሪካዎች እየተገነቡ መሆናቸውንም አብራርተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት 3.4 ሚሊዮን ዳቦ መጋገር የሚያስችል አቅም ተፈጥሯል ብለዋል፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል

ሰኔ 07 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *