በጋምቤላ የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር መንግስት እያጣራው እገኛለሁ አለ፡፡

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት በጋምቤላ የተከሰተው የፀጥታ ችግር ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን እያጣራ እንደሚገኝ ለኢትዮ ኤፍኤም አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል የክልሉ መንግስት ከደቂዎች በፊት ባወጣው መግለጫ በጋምቤላ ከተማ የሸኔ ወታደሮች እና የጋምቤላ ነፃነት ግንባር በጋራ በመሆን ከፍተው የነበረው ተኩስ በአሁኑ ሰዓት መጠነኛ መረጋጋት ገልጻል፡፡
የከተማው ህብረተሰብ ከቤት ባለመውጣት የፀጥታ ሀይሉ እያደረገ ላለው የህግ ማስከበር ተግባር የበኩሉን እንዲወጣ ተጠይቋል።

የደረሰው ጉዳት በውል እንደማይታወቅ የገለፀው የክልሉ መንግስት በሁለቱም ወገን ላይ ጉዳት መድረሱን አስታውቋል።

የመንግስት ኮመኒኪኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሪት ሰላማዊት ካሳ ለኢትዮ ኤፍኤም እንደተናገሩት በክልሉ የተከሰተውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት እያጣራን እንገኛለን ያሉን ሲሆን መረጃውን አጣርተን ስንጨርስ ለህዝብ ይፋ እንዳርጋለን ሲሉ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡

በጋምቤላ ከተማ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ልውውጥ ዛሬ ማለዳውን በታጣቂዎች መከፈቱንና የከባድ መሳሪያ ድምፅ እየተሰማ መሆኑን የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች በስልክ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡

በተለይም በከተማዋ ፤ጎንደር ሰፈር ተብሎ አካባቢና በሌሎችም ቦታዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ድምፅ እየተሰማ መሆኑን ነዋሪዎች ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡

የከተማዋ ነዋሪዎች የተኩስ ልውውጡ ምናልባትም የጋምቤላ ነፃነት ግንባርና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ኦነግ በጋራ በመሆን በብልፅግና መንግስት ላይ እያካሄዱት ያለው ዘመቻ እንደሚሆን አስተያየታቸውን ሰተውናል፡፡

በዚህም ምክንያት ከቤታቸው መውጣትም ሆነ መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ ነግረውናል፡፡
በክልሉ የሚንቀሳቀሰውና የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) የተባለው ፓርቲ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፅ እንዳሰፈረው ፤

የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) እና ኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በ ጋምቤላ ዋና ከተማ ውስጥ የተደረገ ያለው operation የብልጽግና መንግሥት ሰራዊት ተቋማት፣ የብልጽግና መንግስት አመራሮች እና ሰራዊት መሰረት ያደረገ ስለሆነ ፣ማንኛውም ስቭል ማይበረሰብ የበራር ጥይቶች ሰለባ እንዳይሆኑ ከቤቱ እንዳይ ወጣ በጥብቅ እናሳስባለን ሲል ገልፃል፡፡

በኢትዮጲያ ውስጥ የሚሰሩ የማህበራዊ አንቂዎችና የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በጉዳዩ ላይ በሰሩት ዘገባ በጋምቤላ ከተማ ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ ታጣቂዎች የክልሉ ርእሰ መስተዳደር አቅራቢን ለመያዝ ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ልውውጥ እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ የክልሉን ከፍተኛ ሃላፊዎች ጋር ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በተደጋጋሚ ኢትዮ ኤፈኤም ቢደውልም ሊሳካ አልቻለም፡፡

በውልሰው ገዝሙ

ሰኔ 07 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *