የተለያየ ሙያ ኖሯቸው የስራ እድል ላጡ ሰዎች በር የሚከፍት መተግበሪያ ይፉ ሆነ።

“ምን ልታዘዝ አዲስ”የተሰኘው መተግበሪያ የባለሙያ አቅርቦት እና ማንኛውንም አገልግሎቶችን በፍጥነት እንዲያገኝ የሚረዳ ነው ተብሏል ።

ዋና ስራ አሰፈፃሚው አቶ ሱራፌል ተምትሜ እንዳሉት ለረጅም ጊዜ ለማህበረሰቡ ምን ያህል ጠቀሜታ ይሰጣል በሚል ሰፊ ጥናት ተደርጎበታል ።

ከተደራሽነት አንፃር ሁሉንም የሙያ ዘርፍ እና ተቋማትን ተደራሽ ያደርጋል የቸባለ ሲሆን፣ባለሞያዎች ሳይንገላቱ እና አገልግሎቶች ሳይስተጓጎሉ ስራዎች እንዲሳለጡ ያደርጋል ተብሏል ።

አገልግሎቱን መጠቀም የሚፈልጉ ተቋማትም ሆኑ ባለሞያዎች መተግበሪያውን በማውረድ መመዝብ ካልሆነም በ “625” ላይ መደወል እንደሚችሉ ተገልጿል።

ከዚያም በኃላ ደንበኞች በፈለጉበት ሆነው በሙያቸው ወደ ስራ መሰማራት እና አገልግሎት ፈላጊዎች የፈለጉትን ማግኘት ይችላሉ ።

ከአገልግሎቶች መካከል ፣የዲሽ ስራ፣ቲቪ እና ፍሪጅ ጥገና ፣የብየዳ ስራ ፣የቀብር ማስፈፀም እና ሌሎችም በረካታ አገልግሎቶች ተካተዋል።

ከነዚህም በተጨማሪ አገልግሎቱ ለግንባታው ዘርፍ ትልቅ አቅም ይፈጥራል ተብሏል።

በመሳይ ገ/መድህን

ሰኔ 09 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *