14 ጊዜ የሎተሪ እጣ የወጣላቸው ኢትዮጵያዊ!

በኢትዮጵያ የሎተሪ እጣ ታሪክ በተደጋጋሚ የሎተሪ እጣ አሸናፊ በመሆን አቶ መሀመድ አብደላን የሚስተካከላቸዉ የለም፡፡
የጎንደር ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ መሀመድ አብድላ 14 ጊዜ የሎሪ እጣ አሸናፊ መሆን ችለዋል፡፡
ይህም በድርጅቱ ታሪክ በርካታ ጊዜ የሎተሪ እጣን በማሸነፍ ቀዳሚ ያደርጋቸዋል፡፡

አቶ መሀመድ ለእድል የተፈጠሩ ሰዉ ናቸዉ በሚያሰኝ ሁኔታ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ካወጣቸው እጣዎች መካከል 14ቱ እርሳቸው ጋር አርፏል፡፡

አቶ መሀመድ ከብር 500 ጀምሮ እስከ እስከ 750 ሽህ ብር ድረስ በተላያዩ ጊዜያት በመሸለም በኢትዮጵያ ታሪክ ቀዳሚ መሆን ችለዋል፡፡

ግለሰቡ የመጀመሪያ እድል ቤታቸውን ያንኳኳው ጥር 13 ቀን 1980 ዓ.ም በመደበኛ ሎተሪ የ500 ብር አሸናፊ በመሆን ነበር፡፡

ከዚያም በ2007 ዓ.ም ከደረሳቸዉ ዉስጥ ከፍተኛውን የሎተሪ እጣ ማለትም 750ሺህ ብር አሸናፊ መሆን ችለዋል፡፡

አቶ መሃመድ በተደጋጋሚ የሚናገሯት አባባል አለቻቸዉ “በህይወትና በሎተሪ ተስፋ መቁረጥ አያስፍልግም” የሚል፡፡
አቶ መሀመድ ነዋሪነታቸው በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ሲሆን እስካሁን ድረስም ህይወታቸዉን የሚመሩት በልብስ ስፌት ነዉ፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 09 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *