የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ከአፋር ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እራሱን ማግለሉን አስታወቀ፡፡

ፓርቲው በአፋር የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የተሠሰጠውን መግለጫ ውድቅ ስለማድረግ በመገፀበት መግለጫው በጋራ ምክር ቤቱ ላይ ያለው ቅሬታም የገለጸ ሲሆን የጋራ ምክር ቤቱ ከተቋቋመበት እለት ጀምሮ ከተቋቋመለት አላማ በሚቃረን መልኩ ስራ መጀመሩንም ገልፃል፡፡

ይህም በተደጋጋሚም እንዲታረም ብንጠይቅም ጆሮ ዳባ ልበስ ሆኖ አሁን ደርሷል ሲል ፓርቲው መግለጫውን አክሏል፡፡

የጋራ “ም/ቤቱ” በሰኔ 2/ 2014 ባወጠው መግለጫም የአፋር ህዝብ ፓርቲን አቋም የማይገልፅ መግላጫን ሰቷል ሲል ፓርቲው በምክር ቤቱ ላይ ያለውን ቅሬታ አትቷል፡፡

ፓርቲው በምክር ቤቱ ላይ ያለውን ቅሬታና እራሱን ያለለበትን መንገድ ሲገልፅ ምክር ቤቱ ሁለት መሰረታዊ ችግሮች አሉበት ብለን እናምናለን እነዚህም አንደኘው እኛ ስለመግለጫው የምናውቀው አንዳችም ነገር አለመኖሩ ሲሆን ሁለተኛው በቁጥር 7 የተገለፀው ነጥብ ከአቋማችን ጋር የሚጋጭ ሆኖ አግኝተኗል ብሏል፡፡

የአፋር ህዝብ ፓርቲ 04/10/2014 ዓ.ም ጀምሮ ከጋራ ምክር ቤቱ ራሱን ያገለለ መሆኑንም ገልፆ የክልሉ መንግስትም ሆነ ሚዲያም የም/ቤቱን መግለጫም ሆነ ስም በሚጠቅስበት ወቅት አርማችን እና ስማችንን እንዳይጠቀም እናሳስባለንም ብሏል፡፡

በየዉልሰዉ ገዝሙ

ሰኔ 10 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *