ከሀምሌ 1 ጀምሮ ሁሉም ክልሎች ወደ ኦንላይን ትግበራ እንዲገቡ ትዕዛዝ መሰጠቱን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከፊታችን ሀምሌ 1 ጀምሮ ሁሉም ክልሎች ወደ ኦንላይን ትግበራ እንዲገቡ ትዕዛዝ መሰጠቱን በንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ምዝገባና ፍቃድ ደንበኞች አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ጅራታ ነመራ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡

በክልል ደረጃ እስከ ወረዳ ድረስ ይህንን የኦላይን ትግበራ ከህዝቡ ጋር ለማላመድ ወደ አንድ አመት ጊዜ መፍጀቱን ገልፀዋል ።
ምን ያህሉ የህብረተሰብ ክፍል ነው ይህንን የኦንላይን ፕላትፎርም ተጠቅሞ ንግድ ፍቃድ ማውጣት ወይም ማሳደስ የሚችለው የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ወደ አንድ አመት ጊዜ መፍጀቱን አንስተዋል ።

ይህን ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር ከተጠቃሚው ብቻ ሳይሆን ከአገልግሎት ሰጪውም ጭምር ችግሮች ነበሩ ያሉት ዳይሬክተሩ ፣የነበረው አሰራር ለሙስና የተጋለጠ ስለነበር ብዙዎች እንዲቀየር ፍላጎት አልነበራቸውም ብለዋል ።

ብዙ ቁጥር ያለው የንግዱ ማህበረሰብ አነስ ያለ የትምህርት ደረጃ ላይ ነው ያለው ያሉት አቶ ጂራታ ፣ በመሆኑም ይሻላል የምንለውን ቀላል አሰራር አዘጋጅተናል ብለዋል ።

በፌደራል ደረጃ መቶ በመቶ ወደ ኦንላይን ትግበራ ከተገባ ከዓመት በላይ እንደሆነዉም ተናግረዋል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ሰኔ 22 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *