“በአቅርቦት ምክንያት የተፈጠረ ምንም አይነት የናፍጣ እጥረት የለም”–የኢትዮጲያ ነዳጅ አቅራቢ

የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አሁን ስላለው የናፍጣ አቅርቦትን በተመለከተ ከኢትዮ ኤፍኤም ጋር ቆይታ ያደረጉ ሲሆን በአንዳንድ አካላት የነዳጅ አቅርቦት እጥረት እንዳለ የሚገለፀው ከእውነት የራቀ ነው ብለዋል::

ያለፉትን ስድስት ወራት የነዳጅ አቅርቦት አሃዛዊ መረጃ የያዘን ሰነድ ለጣቢያችን ያጋሩት አቶ ታደሰ ኃ/ማርያም፣ ከቀደሙት ወራት ሁሉ የበለጠ በዚህ ወር የናፍጣ አቅርቦት ተደልጓል ብለዋል፡፡

አቶ ታደሰ አቅራቢ ድርጅቱ ከማቅረብ ባለፈ ለተቆጣጣሪ አካላት የተጫነውን የነዳጅ ዝርዝር የያዘን መልእክት የሚያደርስ መሆኑን ጠቁመው ምላሽ ግን እንደማይሰጥ ገልፀዋል፡፡

አሁን ስላለው የናፍጣ ችግር በየደረጃው ያለው ተቆጣጣሪ አካል አስፈላጊውን ቁጥጥር እንዲያደርጉም አደራ ብለዋል፡፡
ዋና ስራ አስፈፃሚው በያዝነው ሰኔ ወር ከዚህ ቀደም ይቀርብ ከነበረው ተጨምሮ በአጠቃላይ ከ 9 ሚሊየን ኪዩቢክ ሊትር በላይ ናፍጣ መቅረቡን ነግረውናል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር
ሰኔ 28 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *