አሜሪካ በኦሮሚያ ክልል ለደረሰዉ ጥቃት ተጠያቂነት እንዲኖር ጠየቀች፡፡

በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኢምባሲ እንዳስታወቀዉ፣ ለደረሰዉ ሰብአዊ መብት ጥሰት ሙሉ ተጠያቂነት እንዲኖር እንጠይቃለን ብሏል፡፡
በኦሮሚያ ክልል በደረሰው አሰቃቂ ጥቃት አዝነናል ያለዉ ኢምባሲዉ ፤ ለተጎዱት ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን ሲል በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል፡፡

ኢትዮጵያዉያን ሁከትን እንዲተዉ፣ በአገሪቱ የሚነሱትን የትጥቅ ግጭቶችን ሁሉ ለማስቆም ውይይት እንዲያደርጉም አሳስቧል፡፡

የአሜሪካ መንግስት በኦሮሚያ ክልል ለደረሰዉ ሰብአዊ መብት ጥሰት ሙሉ ተጠያቂነት እንዲር እንደሚፈልግም ኢምባሲዉ አስታዉቋል፡፡

በአባቱ መረቀ
ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *