የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በወቅታዊ የፀጥታ እና በንጹሐን ዜጎች ጉዳይ ላይ ተወያይቶ የውሳኔ ሐሳብ አሳለፈ::

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች 6ኛው ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛው ልዩ ስብሰባ፤ በወቅታዊ የፀጥታ እና በንጹሐን ዜጎች ጉዳይ ላይ ተወያይቶ የውሳኔ ሐሳብ አስተላለፈ።

የዕለቱን መርኃ-ግብር በግፍ ለተጨፈጨፉት ዜጎች የአንድ ደቂቃ የኅሊና ጸሎት በማድረግ የጀመረው ምክር ቤቱ፤ የሚከተሉትን የውሳኔ ሐሳቦች አስተላልፏል፡፡

በዜጎች ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ እጅግ የኮነነው ምክር ቤቱ፤ በአገራችን በየትኛውም ክልልና አካባቢ በሲቪል ዜጎች ላይ የሞትና የአካል ጉዳት ያስከተሉ እና ንብረት ያወደሙ ግለሰቦች በሕግ እንዲጠየቁ እንዲደረግ ሲል ውሳኔ አሳልፏል።

በየደረጃው ያለው አመራር አካል፣ የጸጥታ አካል እና የፍትሕ ተቋም የህዝቡን ደህንነትና ሠላም በጥብቅ እንዲያስከብር፣ አጥፊዎች ለሕግ ተጠያቂነት እንዲቀርቡ እንዲደረግ ወስኗል።

ከመንደራቸውና ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ የማቋቋም ስራ በአስቸኳይ እንዲሰራ የወሰነው ምክር ቤቱ፤ የኢትዮጵያ ህዝቦች በዚህ በአስቸጋሪ ወቅት ከየትኛውም ጊዜ በላይ በወንድማማችነት፣ በአብሮነት እና በአንድነት እንዲቆሙ መልዕክቱን አስተላልፏል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *