የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ሲሰጥ የነበረው የ2014 ዓም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
በፈተና አሰጣጥ ሂደት ላይም ምንም አይነት ችግር እንዳላጋጠመ የትምህርት ሚኒስቴር ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል ገልፀዋል።

የክልል እና ከተማ አስተዳደር ቢሮዎችም ፈተናው በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የድርሻቸውን ለተወጡ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በተሳካ ሁኔታ ለመስጠት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ስራ አስፈጻሚዋ ገልፀዋል።

የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 27/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 01 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *