የስሪላንካዉ ፕሬዝዳንት ስልጣናቸዉን ለመልቀቅ መስማማታቸዉ ተሰማ::

የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት እንዳስታወቀዉ ፕሬዝዳንቱ ስልጣን ለመልቀቅ ፍቀዳኛ ሆነዋል፡፡
የስሪላንካዉ ፕሬዝዳንት ጎታባያ ራጃፓክሳ የህዝቡ አመጽ ሲበረታባቸዉ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ራኒል ዊክሪሜሲንጊ ስልጣኔን ብለቅ ይሻለኛል እንዳሏቸዉ ተሰምቷል፡፡

ሀገረ ስሪላንካ በተቃዉሞ እየተናጠች ትገኛለች፡፡
ህዝቡም በነቂስ ወጥቶ የአገሪቱን ቤተመንግስት ሙሉበሙሉ ተቆጣጥሮታል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩና ፕሬዝዳንቱ ከስልጣን ካልወረዱ በስተቀር ከቤተ መንግስት እንደማይወጡ ተቀዋሚዎቹ አስታዉቀዋል፡፡
ስሪላንካን ለእንዲህ አይነቱ ነዉጥ የዳረጋት መንግስት የኑሮ ዉድነቱን አላረጋጋም በሚል እንደሆነ አልጄዚራ አስነብቧል፡፡

በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 04 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *