የቀድሞው የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ፓርቲ በሞታቸው ማግስት በተደረገው ምርጫ አሸናፊ መሆኑ ተሰማ፡፡

ሺንዞ አቤ የነበሩበት የጃፓን ሊበራል ዲሞክራሲ ፓርቲ 63 የምክር ቤቱን ወንበር ይዞ ማሸነፉን አረጋግጧል፡፡
የጃፓን የላይኛው ምክር ቤት 125 መቀመጫዎች ያሉሰት ሲሆን ከግማሽ በላይ የሚሆነው በሊበራል ዲሞክራሲ ፓርቲው ዳግም መያዝ ችሏል፡፡

የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ከባድ አደጋ ቢያጋጥመንም በጋራ የተሳካ ምርጫ ማካሄድ ችለናል ሲሉ መናገራቸው ተዘግቧል፡፡
ፓርቲው የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር መገደል ተከትሎ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኘ ሲሆን ለድሉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቶለታል ነዉ የተባለዉ፡፡

የአቤን መገደል ተከትሎ የደህንነት ጥበቃ የሳሳ ነበር ተብሎ ፖሊስ በብርቱ የተተቸ ሲሆን ፖሊስ ጉዳዩን በጥብቅ እንደሚመረምር ቃል መግባቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር
ሐምሌ 04 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *