የጌዶኦ ዞን ባለሁለት እግር ሞተሮኞች እንዳይንቀሳቀሱ ታገደ፡፡

የጌዲኦ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ በዞኑ ስምንት ወረዳዎች አምስት የከተማ አስተዳደሮች ውስጥ የባለሁለት አግር ሞተሮኞች ከትናንት ጀምሮ እንዳይንቀሳቀሱ አግዷል፡፡
መምሪያው እግዱን የጣለው የጌዲኦ ብሄር ራሱን በቻለ ክልል እንዲደራጅ የሚጠይቅ ህዝባዊ ሠልፍ እንዲሚካሄድ በበርካታ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ጥሪ እየተላለፈ መሆኑን ተከትሎ ነዉ፡፡

በዞኑ አሁንም ሰላማዊ ሁኔታ መኖሩን ለዶቼ ቬለ DW በስልክ የገለጹት የጌዲኦ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ አቶ አበባየሁ ኢሳያስ በሞተረኞች ላይ እግዱ የተጣለው ለጠላት ሴራ ያለውን ተጋላጭነት ለመቀነስ ነው ብለዋል፡፡

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *