የሲራላካ ወታራዊ ሀይል የተቃውሞ ካምፖችን ወሯል ..የተቃውሞ መሪዎችንም ማሰራቸው ተሰምቷል፡፡

ተቃዋሚዎች አርብ ማለዳ ላይ ወታደሮች የዋና ከተማዋ ኮሎምቦ አከባቢዎችን ከተቁጣጠሩ በኃላ፣ በአንዳንዱች ላይ ‘በአሰቃቂ ሁኔታ ጥቃት ደርሶባቸዋል’ ብለዋል።
በስሪላንካ የሚገኘው ጦር በተቃዋሚዎች ላይ ጭካኔ በተሞላበት ሆኔታ ድብደባን ከፈጸመ በኋላ በዋና ከተማው የሚገኘውን የፕሬዚዳንቱን ሴክሬታሪያት ተቆጣጥሯል።
በጎታጎጋማ የተቃውሞ ቦታ ላይ በወታደሮቹ በርካታ ድንኳኖች ወድመዋል፣ከ100 በላይ የተቃውሞ ሰልፈኞች ታስረዋል፤ በርካቱችም ተከበዋል ብሏል፤ የአልጀዚራ ዘገባ፡፡
የሲሪላንካው አዲሱ ፕሬዝዳንት ራኒል ዊክርሜሲንግህ በመላው አገሪቱ የሚጸና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸው ብዙዎችን ያስቆጣ ነበር።

ይህን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ተላልፈውታል። በወቅቱ ዊክርሜሲንግህ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተላለፉትን “ፋሺስቶች” ሲሉ ጠርተዋቸዋል።

ፕሬዝደንቱ ጨምረውም ወታደራዊ ኃይሉ የሀገሪቱን ሰላም እና ጸጥታ እንዲያስጠብቅ መመሪያ ማሳለፋቸውን ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ የተጠናከረ የቁጥጥር ስራ እየተሰራ ስለመሆኑ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *