ኢ-ፍትሃዊ ድርጊቶች እየተፈፀመብኝ ነው ሲል የደቡብ ክልል የቁጫ ወረዳ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት ተናገረ።

ምክርቤቱ በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ ሰኔ 14/2313 ዓ.ም በተደረገው ምርጫ የብልጽግናን እና የቁጫ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ጨምሮ ሰባት ፓርቲዎች መሳተፋቸውን አንስቷል።

ነገር ግን ገዢው ፓርቲ በደቡብ ክልል የሚገኘውን የቁጫ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ቁሕዴፓ) መዋቅሩ በወረዳው ተቀባይነት እንዳይኖረው ህዝብ በሰላም እንዳይኖር ኢፍትሃዊ የሆኑ ተግባረትን እያደረገ ነው ብሏል።

የገዢው ፓርቲ አባል ያልሆኑ ግለሰቦችን ማሰር፣ንብረት ማውደም፣ ነጋዴዎች የንግድ ፍቃዳቸው እንዳይታደስ እና የኗሪነት መታወቂያን መከልከል በርካታ እንግልቶች እየተረሰባቸው መሆኑን የቁጫ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና የቁጫ ወረዳ የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት ተወካይ አቶ ገነነ ግደሞ ተናግረዋል።

ይህ ደግሞ ለረጅ አመታት በአብሮነት በኖረ የአከባቢ ማህበረሰብ መካከል የባህል ግጭቶች እንዲነሱ ምክንያት እየሆነ ነው ተብሏል።
ነገር ግን አሁንም በህዝቡ መካከል ግጭት እንዳይነሳ የቻልነውን ሁሉ እያደረግን ነው ሲል የጋራ ምክርቤቱ አሳውቋል።

በርካታ ወጣቶች ለሌላው የፖለቲካ ፓርቲ ድምጽ በመስጠታቸው ምክንያት ለድብደባ ፣ለእስር እና አከባቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል ነዉ ያለዉ የጋራ ምክር ቤቱ።
በዚህም ምክንያት 500 አባወራዎች መኖሪያቸው ለቀው ተሰደዋል ብሏል።
ጉዳዩ ተደጋግሞ ለምርጫ ቦርድ ቢቀርብም ከምርጫ ቦርድ የሚላኩ ባለሞያዎችን እራሱ እያሰረ፣ገዢው ብልፅግና ፓርቲ በወረዳው እንዳሻው እያደረገ ይገኛል ሲል ገዥዉ ፓርቲን ኮንኗል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን
ሐምሌ 20 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *