በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከፍተኛ ድል ያስመዘገበዉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አድናቆት እየተቸረዉ ነዉ፡፡

በአሜሪካ ኦሪገን በተካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በአሥር ሜዳሊያዎች ከዓለም አገራት ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

በሻምፒዮናው ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አራት የወርቅ፣ አራት የብር እና ሁለት የነሐስ ሜዳልያዎችን በማሸነፍ በድላቸው አድናቆት ተችሯቸዋል።

የልዑካን ቡድኑን በመምራት በድል የተመለሰችው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ፤ “በአትሌቶቻችን አገራችን ኮርታለች” ስትል ተናግራለች።

በአሜሪካዋ ግዛት ኦሬገን በተካሄው የአለም ሻምፒዮና ታሪካዊ ውጤት ያስመዘገበው የአትሌቲክስ ቡድን አዲስ አበባ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን አሁንም በተለያዩ የመድናዋ መንገዶች በመንቀሳቀስ ደስታዉን ከከተማ ነዋሪዎች ጋር እየገለጸ ይገኛል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 21 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *