ካለቤ ፋውንዴሽን ላለፉት 6 አመታት ከ850 በላይ አቅመ ደካማዎችን እና ህፃናትን ተጠቃሚ አድርጊያለሁ አለ።

በኢትዮጵያ 2008 ላይ ስራውን የጀመረው የካሌቤ ፋውንዴሽን ግብረሰናይ ድርጅት ላለፉት 6 አመታት ከ850 በላይ አቅመ ደካማ እናቶች እና ህፃናትን ተጠቃሚ አድርጓል ተብሏል ።

የካሌብ ፋውንዴሽን መስራች የሆኑት ወ/ሮ ጤናዳም አለሙ አላማችን ትውልድ ከልመና እና ከተረጂነት ስነ ልቦና ወጥቶ እራሱን በኢኮኖሚው እንዲችል ነው ብለዋል።

ታዲያ ይህን እቅዳችንን ለማሳካት ፤አቅመ ደካማ እናቶችን በቋሚነት እራሳቸውን እንዲችሉ የማድረግ እና መማር የሚገባቸውን ህፃናት በትምህርት ገበታቸው እንዲቆዩ ማድረጋቸውን ገልፀዋል ።

በስድስት አመት ጉዟቸውም ውስጥ ከ850 በላይ አቅመ ደካማ እናቶች እና ህፃናትን ተጠቃሚ መድረግ የተቻለ ሲሆን 6 ተማሪዎች ዩንቨርሲቲ ገብተው ሁለቱ ተመርቀው መጥተዋል ብለዋል ።

ከዚህም በተጨማሪ ልጆቻቸውን ተሸክመው አስቸጋሪን የስራ ጊዜን የሚያሳልፉ እናቶች፣ልጆቻቸውን አስቀምጠው የሚሄዱበት ነፃ የህፃናት ማቆያ ስፍራን ማዘጋጀት እና ወጣቶች ሙያን መማር የሚችሉበትን እድል መፍጠር ተችሏል ነው ያሉት ።

በሃገሪቱ በነበረው ጦርነት ምክኒያት ከመኖሪያ ስፍራቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች 240ሺ ዶለር ድጋፍ ተደርጓል ።

ነገር ግን ከዚህም በላይ ስራዎች መስራት ይቻል ነበር ያሉት የፉውንዴሽኑ መስራች ፤ፋውንዴሽኑ የራሱ መንቀሳቀሻ በጀት አለመኖሩ እና በቂ የማስታወቂያ ስራዎች አለመሰራታቸው ከዚህ ከፍ ባለ ደረጃ እንዳይሰራ አድርጓል ብለዋል።

ጨለማ ውስጥ በነበርንበት ሰአት ካሌብ ፋውንዴሽን አለውላችሁ ብሎ ሕይወታችንን ብሩህ አድርጎታል የሚሉት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የነበሩ ሰዎች መንግስትም ሆነ ሌሎች ተቋማት ከጎኑ እንዲቆሙ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ።

የካሌብ ፋውንዴሽን ለተረጂ ተማሪዎች የሚሆን የዲጅታል ላይብረሪ ለመክፈት እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝም ሰምተናል።

ፋውንዴሽኑ ተግባሩን ለሚያከናውንበት ቢሮ በወር 30 ሺ ብር ኪራይ ይከፍላል ያሉት ወ/ሮ ጤናዳም አለሙ መንግስት የመስሪያ ቦታ ሰጥቶን ከዚህ ተግባር ጎን እንዲቆም ሲሉ ጠይቀዋል ።

በመሳይ ገ/መድህን

ሐምሌ 23 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *