ሱዳን የመጀመሪያዉን የዝንጀሮ ፈንጣጣ ታማሚ ማግኘቷን አስታወቀች፡፡

የሱዳን ጤና ሚኒስትር እንዳስታወቁት ሀገሪቱ የመጀመሪያዉን የዝንጀሮ ፈንጣጣ ተጠቂ አግኝታለች፡፡

ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገጻቸዉ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት አንድ በምዕራብ ዳርፉር የሚኖር የ16 ዓመት ተማሪ በበሽታዉ መጠቃቱን ጽፈዋል ሲል ሮይተርስ ነዉ የዘገበዉ፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት ይፋ ባደረገዉ ሪፖርት፣ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ እስካሁን በ78 አገራት ከ16 ሺህ በላይ በሚሆኑ ሰዎች ላይ ተገኝቷል።

እስከ ትናንት ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች የሞቱት አፍሪካ ውስጥ ብቻ ነበር።

በትናንናዉ እለት ግን ከአፍሪካ ውጭ ለመጀመሪያ ጊዜ ስፔን እና ብራዚል በበሽታው የተያዙ ሰዎች እንደሞቱባቸው ሃገራቱ ሪፖርት አድርገዋል።

አፍሪካ እስካሁን የበሽታው መከላከያ ክትባቶች በእጇ እንዳልገቡ ሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ሐምሌ 25 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *