የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የክስ መቃወሚያ ውድቅ ተደረገ፡፡

ዛሬ ማክሰኞ ሐምሌ 26 ቀን 2014 የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 1ኛ ፀረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች ችሎት አቃቤ ህግ ባቀረበው ክስ ላይ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ካቀረበው መቃወሚያ ጋር አገናዝቦ ብይን ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ ጉዳዩ በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ መሠረት የሚታይ ቢሆንም ይርጋ እንዴት መቆጠር አለበት የሚለው ጉዳይን በወንጀል ህጉ መሠረት ስናየው ክሱ በይርጋ ቀሪ የሚሆን አይደለም በማለት የጋዜጠኛ ተመስገንን መቃወሚያ ውድቅ አድርጎታል።

ፍርድ ቤቱ ክሱን ከቀረበው ማስረጃ አንፃር መርምሮ እንዲከላከል ወይም በነፃ ለመልቀቅ ለነሐሴ 19 ቀን 2014 ቀጠሮ መስጠቱን ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ፅሁፍ አስታውቋል።

ሐምሌ 26 ቀን 2014 ዓ.ም

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *