በኢትዮጵያ ልጆቻቸውን እስከ 6 ወር የጡት ወተት ብቻ የሚያጠቡ እናቶች 59 በመቶ የሚሆኑት ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ በ2012 በተሰራው ጥናት ልጆቻቸውን እስከ 6 ወር የእናት ጡት ወተት የሚሰጡ እናቶች 59 በመቶ ብቻ መሆናቸው በጤና ሚኒስቴር የእናቶች እና ህፃናት ጤና ዳይሬክተር ዶ/ር መሰረት ዘላለም ተናግረዋል።

ይህም ማለት ከሁለት እናት አንዷ ብቻ በትክክል ለልጇ የጡት ወተት ብቻ እንደምትሰጥ ያሳያል።

ለልጆች በተለይም 1000 ቀናትን የጡት ወተት መስጠት ከመመገብ ባለፈ እንደ መጀመርያ ክትባት ነው ብለዋል።
ይህ ተግባራዊ እንዳይሆን ግን በተለይም የዱቄት ወተቶች የሚሰሩላቸው ማስታወቂያ ህጉን የተከተለ አደለም ትኩረት ሊሰጥበት ይገባል ብለዋል።

ከትናንት ሐምሌ 27 ጀምሮ እስከ ነሀሴ 1 ድረስ “ምቹ ሁኔታ ለሚያጠቡ እናቶች ” እናስተምር እንደግፍ በሚል መሪ ቃል በአለም ለ30ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ14 ጊዜ እየተከበረ ይገኛል።

የአለም የጤና ድርጅ መረጃ እንደሚያሳየዉ፣ በዓለም ከሚገኙ ሕጻናት 50 በመቶዉ የእናት ጡት ወተት ብቻ ከተመገቡ ለቀጣይ 10 ዓመታት የ520 ሺህ ልጆች ሕይወት ከሞት ማትረፍ እንደሚቻል ያመለክታል፡፡

በረድኤት ገበየሁ
ሐምሌ 28 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *