ቡና ባንክ በይቆጥቡ ይሸለሙ መርሀ-ግብር ዕድለኛ ለሆኑ መምህራንና የጤና ባለሙያዎች የተለያዩ ሽልማቶችን ሰጠ::

ባንኩ ከመምህራንና ከጤና ባለሙያዎች በተጨማሪም በውጭ ምንዛሬ ይቀበሉ ይመንዝሩ መርሐ ግብር አሸናፊዎችንም ዛሬ ሸልሟል።

የቡና ባንክ በሁለተኛው ዙር የመምህራንና የጤና ባለሙያዎች እንዲሁም የ10ኛ ዙር የይቀቡ ይመንዝሩ ሁለት አሸናፊዎች የቤት አውቶሞቢል ተበርክቶላቸዋል።

ከቤት አውቶሞቢል ሽልማት በተጨማሪም ለሌሎች ባለዕድለኞች የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በዛሬው ዕለት ሰጥቷል።

በ10ኛው ዙር የውጭ ምንዛሬ የይቀበሉ ይመንዝሩ መርሃ-ግብር 30 ደንበኞች ዕድለኛ መሆናቸው ታውቋል።

የቡና ባንክ የማርኬቲንግና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አባይነህ ሀብቴ ቀጣይ መሰል መርሐ ግብሮች እንደሚከናወኑ አስታውቀዋል።

በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 28 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *