ቻይና ወደ ታይዋን ሚሳዔል ማስወንጨፍ ጀመረች::

ቻይና ከዚህ በፊት ከነበሩት ሁሉ ከባድ ነዉ የተባለዉን ልምምድ እያደረገች ሲሆን ፣ ወደ ታይዋንም ሚሳዔል ማስወንጨፏ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

የአሜሪካ ኮንግረስ አፈጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ወደ ታይዋን ጉብኝት አድርገዉ ከተመለሱ በኋላ፣ ቻይና ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሚሳዔሎችን ወደ ታይዋን እያስወነጨፈች መሆኑን ሮይተርስ ነው የዘገበዉ፡፡

የታይዋን መከላከያ ሚኒስቴር ቻይና ወደ ደሴቲቷ 11 ዶንግፌንግ ባለስቲክ ሚሳዔሎችን ወደ ዉሃ ዳርቻዎቿ ማስወንጨፏን ገልጸዋል፡፡

ቻይና ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ታይዋን ዉሃ ዳርቻዎች ሚሳዔል ያስወነጨፈችዉ በ1996 ነበር፡፡

የታይዋን ባለስልጣናት ጉዳዩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን መርህ የጣሰ ነዉ እንዲሁም ነጻ የአየር እና የባህር ጉዞዎች እንዳይኖሩን ገድቧል በሚል አዉግዘዋል፡፡

የቻናዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሰጡት መግለጫ በእሳት የሚጫወቱ መጨረሻቸዉ አያምርም፣ ቻይናን የሚጻረር ደግሞ በቅርቡ ቅጣቱን ይከናነባል ማለታቸዉ ይታወሳል፡፡

እስከዳር ግርማ
ሐምሌ 28 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *