የአንታርክቲካ የበረዶ ግግር በሚያስደንግጥ ሁኔታ እየቀለጠ እንደሚገኝ ሳይንቲስቶች አስታወቁ፡፡

የናሳ ፕሮፐርሽን ላቦራቶሪ ተመራማሪዎች የበረዶ ግግሩ ከሚጠበቀዉ ፍጥነት በላይ እየተናደ እንደሚገኝ አስታዉቀዋል፡፡
ይህም በተፈጥሮ ከሚሆነዉ በላይ እጥፍ መሆኑንና ባለፉት 25 አመታት በአለማችን ላይ የነበረዉን ትልቁን የበረዶ ንጣፍ ኪሳራ በእጥፍ ይጨምረዋል ተብሏል፡፡

ተመራማሪዎቹ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነዉ የአንርታክቲካ የበረዶ ናዳ የባህር ከፍታ መጨመርን በማፋጠን ስጋት መፍጠሩን አሳስበዋል፡፡
የሳይንቲስቶቹ ግኝት የአንታርክቲካ የበረዶ ግግር ወደ ዉቅያኖስ በመግባት የበረዶ መደርደሪያዉን እየከሰመ እንደሚገኝ የሚያመለክት ነዉ፡፡

የአንታርክቲካ የበረዶ መደርደሪያን ብዛት ከ1997 ጀምሮ በ12 ትሪሊየን ቶን ካለፈዉ በእጥፍ መቀነሱን በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡
የጥናቱ መሪ ቻድ ግሪን ባለፈዉ ሩብ ምእተ አመት የአህጉሪቱ የበረዶ ንጣፍ 37ሺህ ስኩዌር ኪሎሜትር የሚጠጋ ሲሆን ይህም ሲዉዘርላንድን ሚያህል ስፋት እንዳለዉ ገልጸዋል፡፡

ቻድ ግሪን ዉጤቶቹ ብዙ እንደሚሆኑ ገልጸዉ አንታርክቲካ በአለም ካሉት በረዶዎች ሁሉ 88 ፐርሰንት የሚሆነዉን እንደሚይዝ ተናግረዋል፡፡

በቤዛዊት አራጌ

ነሐሴ 05 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *