የአዉሮፓ አገራት ዩክሬንን በመደገፋቸዉ ዋጋ ቢከፍሉም ሩሲያን ድል መንሳት እንዳለባቸዉ የህብረቱ የዉጭ ጉዳይ ኃላፊ ተናገሩ፡፡

የአዉሮፓ ህብረት የዉጭ ጉዳይ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል አዉሮፓዉያን ዩክሬንን በመደገፋቸዉ ዋጋ ቢከፍሉም ጦርነቱን ሩሲያ እንድታሸንፍ ግን እድል ሊሰጡ አይገባም ብለዋል፡፡

ዩክሬንን ማስታጠቅና በገንዘብ መደገፍ አዉሮፓን ዋጋ ቢስከፍልም ከሩሲያ የበላይነት ግን አይበልጥም ሲሉም ቦሬል ተናግረዋል፡፡
ሩሲያ የከፈተችዉ ጦርነት በዩክሬን ላይ ብቻ ሳይሆን በመላዉ አዉሮፓዉያን ላይ ስለመሆኑም ኃላፊዉ መናገራቸዉን ሩሲያ ቱዴይ ዘግቧል፡፡

በአዉሮፓ ህብረት የወደፊት ዕቅድ ላይ አስተያየት የሰጡት ቦሬል፣ ‹‹ሩሲያ ይህንን ጦርነት የምታሸንፍ እና የዩክሬንን ግዛት የምትቆጣጠር ከሆነ እኛ አዉሮፓዊያን አለቀልን ማለት ነዉ›› ብለዋል፡፡

የአዉሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ክረምት እየገባ መሆኑን ተከትሎ የሀይል አጠቃቀማቸዉን እንዲያስተካክሉ የተጠየቁ ቢሆንም አንስማማም የሚሉ ድምጾች ከስፔን ማድሪድ መሰማት ጀምረዋል፡፡

የአዉሮፓ አገራት በቀጣይም ዩክሬንን መደገፋቸዉን እንዲቀጥሉ ጆሴፍ ቦሬል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

እስከዳር ግርማ
ነሐሴ 05 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *