በኬንያ ምርጫ ዊሊያም ሩቶ ማሸነፋቸዉ ቢነገርም የኦዲንጋ ደጋፊዎች ግን ዉጤቱን አንቀበልም እያሉ ነዉ፡፡

ዊሊቀም ሩቶ አምስተኛዉ የኬንያ ፕሬዝዳንት ሆነዉ መመረጣቸዉ ቢገለጽም የራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎች በዉጤቱ እምነት የለንም ማለታቸዉ ተሰምቷል፡፡

የምርጫ ኮሚሽነሩ ዋፉላ ቼቡካቲ የምርጫዉን ዉጤት ቢያወጁም የኦዲንጋ ደጋፊዎች ግን ምርጫዉ አልተጠናቀቀም በሚል ተቃዉሞ እያሰሙ ነዉ፡፡

ከኦዲንጋ ጎን ሆነዉ በምርጫዉ የተወዳደሩት ማርታ ካሩዋ በቲዉተር ገጻቸዉ ላይ ባፈሩት ጽሁፍ ምርጫዉ ገና አልተጠናቀቀም ብለዋል፡፡
ሩቶና ኦዲንጋ አንገት ለአንገት በተናነቁበት በዚህ ምርጫ ዊሊያም ሩቶ 50.49 ድምጽ ሲያገኙ የ77 አመቱ ራይላ ኦዲንጋ ደግሞ 48.5 አግኝተዋል፡፡

በአባቱ መረቀ
ነሃሴ 10 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.