የአዋሽ 90.7 ኤፍ ኤም ሬድዮ ሥርጭት መቋረጡንና ቤቱም መታሸጉን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከድርጅቱ አረጋግጧል፡፡
ሬድዮ ጣቢያዉ የታሸገዉ ከቤት ኪራይ ጋር በተገናኘ ስለመሆኑም ሰምተናል፡፡
ከፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የመጡ አካላት የአዋሽ 90.7 ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያን ከኪራይ ዉል ጋር በተገናኘ እንዳሸገዉ ታዉቋል፡፡
አዋሽ ኤፍ ኤም 90.7 አምባሳደር ሲኒማ ህንጻ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
ድርጅቱ አዋሽ ከመባሉ አስቀድሞ ዛሚ ኤፍ ኤም 90.7 የሚል መጠሪያ እንደነበረዉ የሚታወስ ነዉ፡፡
በአባቱ መረቀ
ነሐሴ 10 ቀን 2014 ዓ.ም











