ቻይና ለጋራ ወታደራዊ ልምምድ ወታደሮቿን ወደ ሩሲያ ልትልክ ነዉ፡፡

በሩሲያ አዘጋጅነት የሚካሄደዉ ይህ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ፣ ከቻይና ዉጭ ህንድ፣ ቤላሩስ፣ ሞንጎሊያ፣ ታጃኪስታን እና ሌሎች ሀገራት የሚሳተፉበት ነዉ፡፡

የቻይና በዚህ ወታደራዊ ልምምድ ላይ መሳተፍ አሁን ካለዉ አለም ዓቀፋዊም ሆነ ክልላዊ ችግር ጋር እንደማይገናኝ የቻይና መከላከያ ሚኒስቴር በመግለጫ አስታዉቋል፡፡

ቻይና በዚህ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ላይ የምንሳተፈዉ ከሩሲያ ጋር በየዓመቱ የሚደረግ የሁለትዮሽ ግንኙነት ስምምነት ስላለን ነዉ ብላለች፡፡

ባለፈዉ ወር ላይ ሩሲያ ከነሀሴ 30 እስከ መስከረም 5 ድረስ የሚቆይ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ልታደርግ ማሰቧን ገልጻ ነበር፡፡

ዓላማዉ በጋራ ልምምድ የሚያደርጉ ሀገራት መካከል ያለዉን ግንኙነት፣ የስትራቴጂክ ትብብር ማጠናከር እንዲሁም ለተለያዩ የደህንነት ስጋቶች መልስ መስጠት የሚቻልበትን አቅም መፍጠር ላይ ያተኮረ ነዉ ሲል መግለጫዉ አክሏል፡፡
በቻይናዉ ፕሬዝዳንት ሺ ዢንፒንግ እና በሩሲያዉ አቻቸዉ ቭላድሚር ፑቲን ዘመን የቤጂንግ እና ሞስኮ ግንኙነት በይበልጥ እያደገ መምጣቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ነሐሴ 11 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.