አንቶኒዮ ጉተሬዝ እና ኤርዶጋን በዩክሬን ከዘለኒስኪ ጋር ሊመክሩ ነው፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እንዲሁም የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲብ ጣይብ ኤርዶጋን ከዘለንስኪ ጋር በዩክሬን ሊመክሩ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

የድርጅቱ ቃል አቀባይ እንዳስታወቁት መሪዎቹ በዩክሬን ጦርነት ዙሪያ ለመወያየት ዋነኛ አጀንዳቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከሃገሪቱ ወደ አፍሪካ ሀገራት የሚላከው የስንዴ ምርት እና የዩክሬን የኒውክሌር ጣበያ ጉዳይ ላይም ውይይት ያደርጋሉ ብለዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፍን ጁጃሪክ እንዳስታወቁት የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌኒስኪ ባቀረቡት ግብዥ መሰረት ነው ለመወያየት የተወሰነዉ ብለዋል፡፡
መሪዎቹ በነገው እለት ማለትም ሃሙስ በዩክሬኗ መዲና ኬቭ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከውይይታቸው የእህል ምርት የሚተላለፍበትን የኦዴሳን ወደብ ይጎበኛሉ ሲሉም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት የሩስያ የመከላከያ ሚኒስትር እና የዩክሬኑ የመሰረት ልማት ሚኒስትር የእህል ምርት በሰላም ከወደቡ እንዲተላለፍ የተናጥል ስምምነት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

ሶስቱ መሪዎች በዩክሬን በሚኖራቸው ቆይታ የዩክሬን ጦርነት እንዲቋጭ ፖለቲካዊ መፍትሄ ያቀርባሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ነሐሴ 11 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.