ኤሎን መስክ ማንችስትር ዩናይትድን ሊገዛ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የአለማችን ቱጃሩ ሰው ኤሎን መስክ የእንግሊዙን ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ ለመግዛት መዘጋጀቱን አስታውቋል።

ኤሎን መስክ በቲውትር ገጹ ላይ ባስተላለፈው መልዕክት ከግሌዘር ቤተሰቦች ክለቡን ሊገዛ መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡

የእንግሊዙ ዴይሊ ሚረር ጋዜጣ ባሳለፍነው የፈረንጆቹ አመት የግሌዘር ቤተሰቦች ማንችስተር ዩናይትድን መሸጥ እንደሚፈልጉና 4 ቢሊዮን ፓውንድ እንደሚፈልጉ አስታውቀው ነበር፡፡

አሁን የቴስላው ባለቤት ኤሎን መስክ ክለቡን መጠቅለል እንደሚፈልግ አስታውቋል ፡፡

ኤሎን መስክ ከዚህ በፊት ቲውትርን በ44 ቢሊዮን ዶላር እንደገዛ ሲወራ መቆየቱ አይዘነጋም፡፡

በውጤት መዋዠቅ ውስጥ የሚገኝው ማንችስተር ዩናይትድ በከፊል የክለቡን ድርሻ ለሌላ ባለሃብት ለመሸጥ እንደተዘጋጀም እየተዋራ ነው የሚገኝው፡፡

ኤሎን መስክ ክለቡን ልገዛው ተዘጋጅቻለሁ ቢልም ከክለቡ በኩል የተነገረ ነገር የለም።

በሄኖክ ወ/ ገብርኤል

ነሐሴ 11 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *