የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስተር በኮቪድ 19 መያዛቸዉ ተረጋገጠ::

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስተር ፉሚዮ ኪሺዳ በኮቪድ 19 መያዛቸዉንና በቤታቸዉ ዉስጥ እያገገሙ እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስተሩ ከቀናት በፊት የኮሮና ምልክት እያሳዩ መሆናቸዉን ተከትሎ ባደረጉት ምርመራ ነዉ በኮሮና መያዛቸዉ የተረጋገጠዉ፡፡

ኪሺዳ ከሳምንታት እረፍ በኋላ ወደስራቸዉ እንደሚመለሱም ነዉ የተነገረዉ፡፡

ሀገረ ጃፓን በኮሮና ወረርሽኝ ማእበል ዉስጥ ባለፉት ሳምንታት ብቻ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሪፖርቶችን በማቅረብ በአለም ላይ ከፍኛዉ አዳዲስ ተጠቂዎች ያስመዘገቡ ሃገራት ዉስጥ መግባቷን የአለም ጤና ድርጅት ማስታወቁን ሲ ጂ ቲኤን ዘግቧል፡፡

በቤዛዊት አራጌ
ነሐሴ 16 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.