ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ በጋራ ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ ጀምረዋል፡፡

ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ በዓይነቱ ትልቅ ነዉ የተባለዉን ወታደራዊ ልምምድ በጋራ መጀመራቸዉ ነዉ የተዘገበዉ፡፡
የሰሜን ኮሪያን ጥቃት ለመቋቋም የሚያስችል አቅም ለመገንባት ሁለቱ ሀገራት በጋራ ልምምድ መጀመራቸዉ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

ወታደራዊ ልምምዱ ለሀገሪቱ ለጦርነት ምላሽ የመስጠት እና አቅም የማጎልበት ሂደትን የሚያጠናክር መሆኑን የደቡብ ኮሪያዉ ፕሬዝዳንት ዮን ሱክ ዮል ተናግረዋል፡፡

‹‹በኮሪያ ሰርጥ ያለዉን ሰላም የማረጋገጥ እና ደህንነት የማስጠበቅ አቅማችን የሚገለጸዉ በዚህ ልምምድ ነዉ›› ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ባለፈዉ ሳምንት ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ ለወታደራዊ ልምምዱ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ በነበረበት ወቅት፣ ሰሜን ኮሪያ ሁለት የክሩዝ ሚሳዔሎችን መተኮሷን ባለስልጣናት ገልጸዋል፡፡

ሰሜን ኮሪያ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በዚህ ዓመት በተከታታይ ሚሳዔል ማስወንጨፏን ያነሳዉ የደቡብ ኮሪያ መንግስት፣ ሰባተኛዉን የኒዉክሌር ሙከራ በማንኛዉም ሰዓት ልታደርግ እንደምትችል እርግጠኛ መሆኑንም ገልጿል፡፡

አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን በቅርቡ የባለስቲክ ሚሳዔል መመከት እና መከላከል የሚያስችል ወታደራዊ ልምምድ በሀዋይ የባህር ዳርቻ ማድረጋቸዉ የሚታወስ ነዉ፡፡

የአሁኑ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ከፈረንጆቹ 2017 ወዲህ የተደረገ ከፍተኛዉ ወታደራዊ ልምምድ መሆኑን ሮይተርስ ነዉ የዘገበዉ፡፡

በእስከዳር ግርማ

ነሐሴ 16 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *