የዘንድሮው የጳጉሜ ፌስቲቫል በእጦጦ ፓርክ ይካሄዳል፡፡

“ጳጉሜ የአፍሪካ ወርቃማ ወር” በሚል መሪ ቃል ከጳጉሜ አንድ እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በእንጦጦ ፓርክ እንደሚካሄድ ታውቋል።

የጳጉሜ አብ ሀገር አቀፍ ፌስቲቫል በሰጠው መግለጫ፣ ፌስቲቫሉ በእንጦጦ ፖርክና በመላው አዲስ አበባ በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበር አስታውቋል።

ፌስቲቫሉ ኢትዮጵያ ያላትን ተፈጥሯዊ ሀብቶቿን ለአለም አቀፉ ማህበረስብ ለማድረስ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለውም ተነስቷል።

ጳጉሜ አንድ የሰላምና የፍቅር ቀን፣

ጳጉሜ ሁለት የባህልና የአፍሪካ ቀን
ጳጉሜ ሦስት የአፍሪካ ለልጆች ክብረ በዓል ወይንም የዝናብ ላይ ሩጫ በሚል እንደሚከበርም ሰምተናል።

እንዲሁም ጳጉሜ አራት እንነግድ በጳጉሜ ፣ጳጉሜ አምስት ደግሞ የጳጉሜ ውቦች በሚል እንደሚከበር ተነግሯል።
ለአምስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ፌስቲቫል ላይ፣ ባዛሮች፣ ስፖርታዊ ውድድሮች፣የሙዚቃ ድግስ፣ የባህል ቁንጅና ውድድሮች እና የምግብ ዝግጅት እንደሚከናወኑ አዘጋጆች አስታውቀዋል።

በአባቱ መረቀ
ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *