ቼልሲ ፎፋናን አስፈርሟል፡፡

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ፈረንሳዊውን የመሃል ተከላካይ በ70 ሚ.ፓ ለሰባት ዓመት በሚዘልቅ ውል በእጁ አስገብቷል፡፡

ለፈረንሳይ ከ21 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን የሚጫወተው ፎፋና ሰን ኤቲዬን ለቅቆ ሌስተር ሲቲን የተቀላቀለው በ2020 ነበር ፡፡

በኪንግ ፓወር ቆይታው በ37 የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ተጫውቷል ፡፡
በ2021 -22 የውድድር ዘመን እግሩ ላይ ባጋጠመው ጉዳት ተሳትፎው በሰባት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ብቻ ተገድቧል ፡፡
‹‹ ያለፉት ሁለት ቀናት ለእኔ ልዩ ትርጉም ነበራቸው ፡፡
በጣም ደስ ብሎኛል ፡፡
ዛሬ ከቡድኑ ጋር ልምምድ ሰርቼያለሁ፡፡ ለደጋፊዎች እና ለክለቡ ለመጫወት ጓጉቼያለሁ ›› ብሏል ፎፋና ፊርማውን ካኖረ በኋላ ፡፡

በአቤል ጀቤሳ

ነሐሴ 25 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *