የጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ በመጪው መስከረም 10/ 2015 ዓ.ም ዕጣ እንደሚያወጣ አስታወቀ

የጎጆ ብሪጅ ሃውሲንግ ትሬዲንግ ከዚህ ቀደም ጳጉሜ 03/2014 ዓ.ም ይወጣል ብሎ የነበረውን የዕጣ ማውጣት ስነሥርዓት ወደ መስከረም 10/2015 ዓ.ም መቀየሩን አስታውቋል ።

ዕጣ የሚወጣበት ጊዜ የተቀየረበት ዋነኛው ምክንያት አዲስ ተመዝጋቢ አባላት ጥያቄ በማቅረባቸውና የአባላቱን ቁጥር ለመጨመር እንደሆነም ተናግሯል ።
ኀየጎጆ ሃውሲንግ ትሬዲንግ ምክትል ዳይሬክተር አቀ ናደው ጌታሁን በሰጡት መግለጫ በዕጣ ማውጣት ስነስርዓቱ ላይ አዲስ የተመዘገቡ 4 መቶ አባላት የሚደራጁበትን ቦታ እንዲያውቁ ይደረጋል ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የጎጆ ሃውሲንግ ያለቁ 4 ሳይቶችና ለማህበራቱ ካርታ ርክክብ እንዲሁም 4 የሳይቶች የግንባታ ፍቃድ ርክክብ እንደሚከናወን አቶ ናደው አስታውቀዋል ።

በዕለቱ ለጤና ባለሙያዎች የመኖሪያ መንደር ለመገንባት ከጤና ሚኒስቴርና ከዳሽን ባንክ ጋር የመግባቢያ ስምምነት እንደሚያደርግም ታውቋል።

የጎጆ ብሪጅ ሃውሲንግ እስካሁን 4 ሳይቶች፣ 8 ማህበራት ፣ እና ከ 1 ሺህ በላይ አባላትን ማፍራት መቻሉም በመግለጫው ተነስቷል።

ጎጆ ብሪጅ ሃውሲንግ በከተማዋ ያለውን የቤት ችግር ለመቅረፍ እየሰራ የሚገኝ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ነው ተብሏል ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *