የማይናማሯ የቀድሞ መሪ አዉንግ ሳንሱኪ በምርጫ ማጭበርበር የ 3 ዓመት ፍርድ ተፈረደባቸዉ፡፡

ይህ የ 3ዓመት ፍርድ ከዚህ በፊት በወታደራዊዉ የማይናማር መንግስት በተፈረደባቸዉ 17 ዓመት የእስር ጊዜ ላይ የሚጨመር ነዉ፡፡

ሳንሱኪ በምርጫ ማጭበርበር ወንጀል የ3 ዓመቱ ፍርድ ከከባድ የስራ ጫና ጋር የተፈረደባቸዉ ሲሆን፣ ከዚህ በፊት በተለያዩ ወንጀሎች ከተፈረደባቸዉ የ 17 ዓመት እስር ላይ የሚጨመር መሆኑም ነዉ የተገለጸዉ፡፡

ሳንሱኪ በ2020 ህዳር ወር ላይ በተደረገዉ ምርጫ ላይ ፓርቲያቸዉ በከፍተኛ የበላይነት አሸንፏል በማለት ምርጫ አጭበርብረዋል ነዉ የተባለዉ ፡፡

በዚህ ወንጀል የተነሳ በተፈረደባቸዉ ፍርድ ሳንሱኪ ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት ከፖለቲካዉ ርቀዉ ይቆያሉ የተባለ ሲሆን፣ ወታደራዊዉ መንግስት በሳንሱኪ ዙሪያ ከዚህ በኋላ የሚከሰዉ እና ለፍርድ የሚያቀርባቸዉ ብዙ ወንጀሎች አሉት ነዉ የተባለዉ፡፡

የኖቤል ሽልማት ተሸላሚዋ እና የማይናማር ተቃዋሚ ፓርቲ ቀንደኛ መሪ አዉንግ ሳንሱኪ ባለፈዉ ዓመት በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን መዉረዳቸዉ የሚታወስ ነዉ፡፡

ወታደራዊ መንግስቱ ወደ ስልጣን ከመጣ ወዲህ በተፈጠሩ ግጭቶች ከ 2ሺህ 200 በላይ የሚሆኑ ዜጎች ህይወታቸዉን ያጡ ሲሆን ፣ ከ 15ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ለእስር ተዳርገዋል ሲል የዘገበዉ አልጀዚራ ነዉ፡፡

በእስከዳር ግርማ

ነሐሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *